“የተጎዳ ሰው ሳይኖር አይቀርም።”
“አዎ። አንዷን ማሽን ጨረፍ አድርጓት. . . .” አለች
“እና ምን አደረጋችሁላት?”
“የወጡት መኪናዎች ይመለሱና ወደ ሆስፒታል ትወሰዳለች” አለች ሥራዋን ሳታቋርጥ።
* * *
“ለመሆኑ ያንቺ ልጆች ጤፍ ምን እንደሚመስል ያውቃሉ?” አለ ከመቀመጫው ተነስቶ ከወይዘሮ ዋላቴ አጠገብ እራቅ እያለ። ሁሉም ሳቁ። “እውነቴን እኮ ነው። እነሱ እኮ በሃገሪቷ ላይ የሚመረተው ስንዴ እና በቆሎ ብቻ ይመስላቸዋል” አለ ደገመና::
* * *
‘’አንዱ ልጅ፣ ሌላው የእንጀራ ልጅ ሆኖ መቼም አይቀር። ቆይ ብቻ!’’ ከማለቷ:
‘’ቆይ ብቻ! ቆይ ብቻ! ቆይ ብቻ!’’ እያለ በማዜም፣ እንዳልክ በትርንጎ ላይ መቀለድ ጀመረ።